አዲሱ የሰዋስው መልቲሚዲያ ፕሮጀክት: የሰዋስው ፖድካስቶች ኔትወርክ
ሰዋስው የፖድካስቶች ኔትወርክ ባለቤትነቱ የቱኤፍ ካፒታል ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር የሆነ፣ በሰዋስው መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ የሚሰራጭ፣ ፈጠራን፣ ግኝትን እና መማማርን የሚያሳድግ ልዩ ዝግጅት ነው። እምቅ አቅም ባለው የኢትዮጵያ ባህል እና ዕውቀት ምህዳር ላይ የተመሰረተ፤ በሀገር ውስጥ እና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተሰሚነት እና ተወዳጅነት ያላቸውን የፖድካስት አቅራቢዎች ይዟል። በውስጡም አዝናኝ፣ መረጃ ሰጪ እና አነቃቂ ዝግጅቶችን ያቀርባል።
ፖድካስቶቻችችን በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች እና ዘውጎች አካቷል። ከእነዚህም መካከል ታሪክ፣ ሥራ ፈጠራ፣ ሙዚቃ፣ ሕግ፣ ስነ፡ልቦና እና ትምህርት ይጠቀሳሉ። እያንዳንዱ የፖድካስት ክፍል የአድማጮችን ቀልብ የሚይዝ እና አውዳቸውን አስፍተው እርስ በርስ እንዲወያዩ የሚያነሳሳ እና የሚጋብዝ ነው።
ሰዋስው የፖድካስቶች ኔትወርክ በኢትዮጵያ የፖድካስት ባህል እንዲያድግ፣ የድምፅ ትረካን በመጠቀም የዕውቀት ልውውጥ እንዲኖርና ምሁራዊ ውይይቶችና ክርክሮች እንዲበዙ እየሠራ ይገኛል። ተሰጥኦን በማሳደግ ህብረ፡ብዙ የሆኑ ሐሳቦች እና ድምፆች እንዲሰሙ ይጥራል። ኢትዮጵያ ታላቅ ዕድገት አስመዝግባ የፈጠራና የፈጣሪዎች መገኛ ምድር እንድትሆን ተግቶ ይሰራል።
የሰዋስው ፖድካስቶች ኔትወርክ በቴክኖሎጂ ፈጠራ በቀዳሚነት በሚጠቀሱት ባለራዕይዎች ይመራል። ቴክኖሎጂን በመጠቀም የትራንስፖርት ዘርፉን ያዘመነው ራይድ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ እና የኢትዮጵያን ሙዚቃ ግብይት ከዓለም እኩል ያራመደው ቱ ኤፍ ካፒታል ከሚመሯቸው በቴክኖሎጂ የታገዙ ስራ ፈጠራዎች መካከል አንዱ ነው። ተቋማቱ እና መሪዎቻቸው የስራ ፈጣሪነትን መንፈስ በመገንባት ኢትዮጵያን የፈጠራ ማዕከል ለማድረግ የሚያዝችል ዘርፈ ብዙ ግዙፍ ፕሮጀክት ነድፈው ወደ ተግባር ገብተዋል። ተደራሽ ግባቸው ኢትዮጵያን “የፈጣሪዎች ምድር” (creative kingdom) እንድትሆን መደላድል መፍጠር ነው።
በትጉህ የሥራ ባልደረቦቻችን፤ ማለትም ፖድካስተሮች፣ ፕርዲዩሰሮች፣ እና የሥራ ፈጣሪዎቻችን እየታገዝን አድማጮቻችንን ለአዎንታዊ ለውጥ እንዲነሳሱ መነሻ ፍንጣቂ የሚሆኑ የድምፅ ጥራታቸው ከፍ ያሉ ዝግጅቶች ይኖሩናል።
እንኳን ወደ ሰዋስው የፖድካስቶች ኔትወርካችን በደህና መጡ፦፦
ድምፆቻችሁ የሚሰሙበት፣ ሐሳቦቻችሁ የሚያብቡበት እና ጥበብን ከነ ሙሉ ክብሯ እና ገናናነቷ የምታገኙበት፤ ሰዋሰው ፖድካስቶች ኔትዎርክ
የሰዋስውን መተግበሪያ በእጅዎ በመያዝ የሰዋስውን ቤተሰብ ይቀላቀሉ
#sewasew
#sewasew_podcasts_network
#sewasewmultimedia
Recent Posts
ሰዋሰው መተግበሪያ ለደንበኝነት አገልግሎት የሚውል 9107 የተሰኘ አጭር ቁጥር አስተዋወቀ
February 8, 2023
የአንባሰሏ ንግሥት የክብር ዶክትሬቷን ከ7 ዓመታት በኋላ ተረከበች
February 8, 2023