በያዝነው ሳምንት የሦስት ሙዚቀኞች ስራ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ይለቀቃል

ሰዋሰው ዜና – ጥር 5/2015 ዓ.ም.

የሙዚቃ ሥራዎችን የሚያገበያየው “ሰዋሰው” መተግበሪያ በ9107 አጭር ቁጥር የክፍያ ደንበኝነት (ፕሪምየም) አገልግሎት መግዛት የሚቻልበትን አማራጭ ማስጀመሩን አስታውቋል። “ሰዋሰው” ከሞባይል አየር ሰዓት ተቀናሽ በሚደረግ ሂሳብ ሳምንታዊ እና ዕለታዊ የደንበኝነት አገልገሎቶችን መግዛት የሚቻልበትን አዲስ አማራጭ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

በመተግበሪያው አማካኝነት የሚለቀቁ ሙዚቃዎችን በክፍያ እና ያለ ክፍያ አማራጮች ያቀረበው “ሰዋሰው” በክፍያ አማራጭ አገልግሎቱን ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ በእናት ባንክ እና በቴሌብር ሲያስከፍል መቆየቱ ይታወሳል። በአሁን ሰዓት ከነበሩት አገልግሎቶች በተጨማሪ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት የሚያስችለውን 9107 አጭር የጽሑፍ መልእክትን አስጀምሯል። አዲሱ አሰራር ደንበኞች እንደ አገልግሎት ምርጫቸው A ወይም B የተሰኙትን የእንግሊዘኛ ፊደላት ወደ 9107 በመላክ ሳምንታዊ ወይም እለታዊ ያለማስታወቂያ ያልተገደበ ሙዚቃ ለማድመጥ የሚያስችላቸውን አገልግሎት ይገዛሉ።

Sewasew 9107

ከ100 በላይ ሙዚቀኞች፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲያን፣ አቀናባሪዎች አብሮ የመስራት ስምምነታቸውን የሰጡት ሰዋሰው። በቅርቡ አልበማቸውን በመተግበሪያው አማካኝነት ለሕዝብ ካደረሱት ግርማ ተፈራ፣ ሔኖክ አበበ፣ ካሙዙ ካሳ፣…. በተጨማሪ ክቡር ዶ/ር ማሪቱ ለገሰን፣ አስቴር አወቀን እና ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮን ማስፈረሙ ይታወቃል።

የሰዋሰው መተግበሪያን አገልግሎት በክፍያ የሚጠቀሙ ደንበኞች የራሳቸውን የማጫወቻ ዝርዝር ‘ፕሌይ ሊስት’ የማዘጋጀት፣ ሁሉንም ሙዚቃዎች ያለ ገደብ እና ያለ ማስታወቂያ የማድመጥ፣ ያወረዷቸውን ሙዚቃዎችን ያለ ኢንተርኔት ግንኙነት የማድመጥ፣… ልዩ ዕድሎች ይኖሯቸዋል።

Igniting Creativity

ከድምጻዊው በተጨማሪ ሁሉም የጥበብ ስራው ተሳታፊዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አዲስ አሰራር ይዞ መምጣቱ ልዩ እንደሚያደርገው የተነገረለት “ሰዋሰው” መተግበሪያ ሌሎች የኪነጥበብ ውጤቶችን የማገበያየት እቅድ እንዳለውም ታውቋል። በመተግበሪያው ከሙዚቃ በተጨማሪ ከድምጸ መጻሕፍት (የመጽሐፍ ትረካ)፣ ፖድካስቶች፣ ተከታታይ ድራማዎች፣ ፊቸር ፊልሞች የሚካተቱ ሲሆን የሰዋሰው መተግበሪያ ባለቤት የሆነው ቱ ኤፍ ካፒታል በተጨማሪ የሁነት ዝግጅት እና ብራንዲንግ ላይ ለመሰማራት የሚያስለውን መደላድል በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Recent Posts