ለምለም ሃ/ሚካኤል
ለምለም ሃይለ ሚካኤል ልዩ ድምፅዋን እና ምርጥ ስራዋን በአለምአቀፍ ደረጃ ለመቀጠል በኢትዮጵያ የሙዚቃ ፕላትፎርም ሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር ተፈራረመች።
የልጅነት ሕይወት
ኣርቲስት ለምለም ሃይለሚካኤል አሸቱ መጋቢት 20 ቀን በባሌ ዞን አርጋፋ ወረዳ ተወለደች። የመጀመሪያ ዲግሪዋን በቲያትር ጥበብ እና ሁለተኛ ዲግሪዋን በቴአትር ፎር ዴቨሎፕመንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አገኘች። በልጅነቷ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መዘመር የጀመረች ሲሆን በቤተሰብ ዝግጅቶች ላይም ዝግጅቷን ታቀርብ ነበር። እንደ መነሻ እንደ አስቴር አወቀ ያሉ ታዋቂ አርቲስቶችን እያየች ያደገች ሲሆን አባቷም እነዚህን ካሴቶች በመግዛት ያበረታታት ነበር።
የሙዚቃ ህይወት
ወደ ሙዚቃ ሙያ የተቀላቀለችው የኛ የተሰኘውን ፕሮጀክት ከተቀላቀለች በኋላ ሲሆን የአሁኑ አልበሟን ለመስራት ብዙ ታዋቂ እና ጥበበኛ አርቲስቶች እና ፕሮዲውሰሮች ተሳትፈውበታል። ይህ አልበም ወደ ሕይወት የመጣው የሥራ ባልደረባዋ በሆነው ወንደሰን ይሁብ አማካኝነት ሲሆን አልበሙን ለመጨረስም አራት ዓመት ገደማ ፈጅቷቸዋል። ለምለም በግልም ሆነ በቡድን ደረጃ የተለያዩ ድንቅ የመድረክ ትርኢቶች ቢኖሯትም የየኛ የመድረክ ትረኢት ከህዝብ ጋር ያስተዋወቃት ስራዋ ነበር።
እዚህ ሙያ ውስጥ ከገባች በኋላ የተገነዘበችው ነገር በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ውስጥ ሙዚቃ ማዘጋጀት እጅግ ከባድ እንደነበረ እና ጀማሪ ሙዚቀኞችም ብዙ ዋጋ ሊያስከፍላቸው እንደሚችል ነው። ቢሆንም ጥንካሬዋን የምትወደው ነገር ላይ በመጠቀም እና ዋጋዎችን በመክፈል ጥሩ የሙዚቃ አልበም ለማዘጋጀት ረጅም ጊዜ ፈጅቶባታል።
ትብብር
ለምለም ከኢትዮጵያ ታላላቅ ሙዚቀኞች ጋር የሰራች ሲሆን የቅርብ ጊዜ አልበሟ ላይ ኤልያስ መልካ፣ አበጋዝ ሼኦታ፣ ሚካኤል ሃይሉ እና ከታምሩ አማረ ተሳትፈውበታል። የቅርብ ጊዜ አልበሟ ላይ በግጥም ወንድወሰን ይሁብ፣ ናትናአል ግርማቸው እና ሃብታሙ ቦጋለ የተሳተፉበት ሲሆን በዜማ ደግሞ ኤልያስ መልካ፣ አንተነህ ወራሽ፣ አህመድ ተሾመ፣ ብስራት ሱራፌል፣ ሃብታሙ ቦጋለ እና እሱባለው ይታየው ተሳትፈውበታል።
የትወና ሙያ
የለምለም ካሏት የተለያዩ ተሰጥኦዎች ውስጥ የትወና ክህሎት አንዱ ሲሆን ከቲያትር ዳይሬክተር አባተ መኩሪያ ጋር ሃገር ማለት የተሰኘ ቲያትር ተጫውታለች። የትወና ህይወቷ ሙያዋ ላይ ከፍተኛ ተጽንዎ በመፍጠሩ አድናቂዎቿ እስካሁን “ሚሚ” በሚል የመድረክ ስም ይጠሯታል። ለምለም በተጨማሪም ትመጣለህ እና አንድ ጀግና የተባሉ ፊልሞችን ከቅርብ ጓደኛዋ ጋር በመሆን አዘጋጅታለች።
ከሰዋሰው ጋር
በመጨረሻም በዚህ ዓመት ያሰበቻቸውን ስራዎቿን ለሕዝብ ለማድረስ ከሰዋሰው ጋር ስምምነት የፈጠረች ሲሆን ከ 5 እስከ 10 ለሚሆኑ አመታት ውስጥ ደግሞ የተሻሉ ስራዎችን ለአድናቂዎቿ ለማድረስ እቅድ ይዛለች።
በቅርቡ…