ብርሃኑ ተዘራ ልዩ ድምፁን እና ምርጥ ስራውን በአለምአቀፍ ደረጃ ለመቀጠል በኢትዮጵያ የሙዚቃ ፕላትፎርም ሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር ተፈራረመ።
የልጅነት ሕይወት
አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ በቀለ በ1971 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካዛንቺስ ሰፈር በተለምዶ በቅዱስ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ተወለደ። የመጀመሪያ አና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮከበ ጸባህ ትምህርት ቤት አጠናቆ ወደ ኮሜርስ በመሄድ የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀበለ።
አርቲስቱ የኢትዮጵያ ሂፕ ሆፕን፣ የሬጌ ሙዚቃን እና ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፈኖችን በመጫወት ይታወቃል። የሙዚቃ ሙያውን ከጀመረ ወዲህ በብዙዎች ዘንድ የታወቀና የተወደደ ሲሆን አሁንም ከኢትዮጵያ ተወዳጅ ሙዚቀኞች አንዱ ሆኗል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መዘመር የጀመረው የ16 ዓመት ልጅ እያለ ሲሆን ከዚያም ከሙዚቀኛ ጌራ ጥበብ ጋር በቀበሌ ኪነት መዝፈን በመጀመሩ የሙዚቃ ሙያ ተሰጥኦ እና ችሎታ እንዳለው ለመገንዘብ ቻለ።
የሙዚቃ ህይወት
እድሜው ሲገፋ የመጀመሪያ አልበሙን (ላ ፎንቴን) ተው አምላኬን በ1988 ዓ.ም. ከሙዚቀኛ ታደለ ሮባ ጋር በመቅናጀት የማዘጋጀት እድሉን አገኘ። ። ይህ ቅጂ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ጥሩ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን የመጀመሪያ አልበሙን ሲጨርስ ወደ ኬንያ ተጉዞ በአራት ክለቦች ከአርቲስት ታደለ ሮባ ጋር ስራዎቻቸውን ለ ታዳሚ ማድረስ ችሏል።
የግል ሕይወት
አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ተግቶ በመስራትና ራሱን፣ ሙያውን እንዲሁም ቤተሰቡን ሚወድ የተከበረ ድምፃዊ ሆነ። እንደ መልካሙ ተበጀ እና አረጋሀኝ ወራሽ ያሉ ታዋቂ አርቲስቶችን ማድመጡ በዚህ ሙያ ውስጥ ብዙ እንዲማር አና አንዲገፋበት ተፅዕኖ አሳድሮበታል። ብርሃኑ ተሰጥኦውን ያከበረ ከመሆኑም በላይ በአሁኑ ጊዜ የተዋጣለት ድምፃዊ ለመሆን በየዕለቱ ይለማመድ ነበር ። እውቁ ዘፋኝ የግል ህይወቱን በሚመለከት ከ ሙዚቃ ወጪ በትርፍ ጊዜው ፊልሞችንና እግር ኳስን መመልከት ይወዳል።
ከመድረክ በስተጀርባ ብዙ አርቲስቶች ሕዝብ የማያስተወለውን ብዙ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሟቸው እንደመሆኑ መጠን አንዳንድ ፈታኝ ጊዜያት እንደነበሩና በሙዚቃ ሙያው መጀመሪያ ላይ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ እንደነበር ተናግሯል ። ከሙዚቀኛ ታደለ ሮባ ጋር ወደ ለንደን ገጠር ሲጓዝ፣ የአውሮፕላን ሞተር ችግር እንደነበረባቸው፣ ይህ በህይወቱ ፈጽሞ የማይረሳው ክስተት እንደነበርም አክሎ ገልጿል።
የሚሊኒየም ትርኢት
እጅግ ክማይረሳው ስራዎቹ መሃል ለኢትዮጵያ ሚሊኒየም በዓል ‹‹ክብሬ ለ ኢትዮጵያ›› በተሰኘው ኮንሰርት ላይ ‹‹ያምቡሌ›› እና ‹‹አንበሳው አገሳ›› የሚሉ ታዋቂ ዘፈኖቹን ለመዝፈን ችሎ ነበር። ጥላሁን ገሰሰ ፣ መሃሙድ አህመድንን እና ቢዮንሴን ጨምሮ ከሌሎች 15 ዘፋኞች ጋር ትርኢት ያቀረበ ሲሆን ሚሊኒየም ላይ ደግሞ ከንዋይ እና ከጂጂ ጋር በዩናይትድ ስቴትስ ስራዎቹን ኣቅርቧል።
ከሰዋሰው ጋር
በመከራና ስኬት ሁሉ አልፎ አርቲስት ብርሀኑ ዛሬ ሁላችንም የምናውቀውና የምናደንቀው ድምፃዊ ሆኖ እዚህ ቢደርስም በዚም ሳያበቃ ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር በመተባበር ወደፊት ግሩም የሙዚቃ ስራዎቹን ለአድናቂዎቹ ለማድረስ በስራው አዲስ ምዕራፍን ጀምሯል።
በቅርቡ…