የሙዚቃ ኢንደስትሪ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቅኝት  የሚባል መሰረታዊ የሞዳል ስርዓት ይጠቀማል። ከነዚህም ውስጥ ትዝታ፣ ባቲ፣ አምባሰል እና አንቺሆዬ የሚባሉ አራት ዋና ዋና ዘዴዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህ  በተጨማሪም ትዝታ ማይነር, ባቲ ሜጀር, እና  ባቲ ማይነር ይኙበታል።.

አንዳንድ ሙዚቃዎች ስሞቻቸውን ከቅኝቶቻቸው የሚወስዱ ሲሆን  በባህላዊ መሳሪያዎች ሲጫወቱ  በትንሹም ቢሆን ከምእራቢዋን ይዘት ይርቃሉ። ይሁን እንጂ እንደ ፒያኖና ጊታር ባሉ የምዕራባውያን የሙዚቃ መሣሪያዎች ላይ ሲጫወቱ ደግሞ በምዕራቡ ዓለም በተለመዱት መሣሪያዎች ይጫወቱ ነበር።

የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአፍሪካ የሙዚቃ ባህሎች ዘንድ በጣም ለየት ያለና ሚስጥራዊ ነው። በኢትዮጵያ ተራራማ አካባቢዎች ሙዚቃ  የሞኖፎኒክ ወይም ሄትሮፎኒክ ባህሪ ያለው ሲሆን በአንዳንድ ደቡባዊ አካባቢዎች ደግሞ አንዳንድ ሙዚቃዎች ፖሊፎኒክ ናቸው።

የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአፍሪካ የሙዚቃ ባህሎች ዘንድ በጣም ለየት ያለና ሚስጥራዊ ነው።

A girl putting on headset with sewasew logo

የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአፍሪካ የሙዚቃ ባህሎች ዘንድ በጣም ለየት ያለና ሚስጥራዊ የነበረ ሲሆን ከ1960ዎቹ ጀምሮ አስደናቂ በሆነ መንገድ ዘመናዊ ሆኖ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንዱስትሪን  ያለበት ደረጃ ለማድረስ  መሐሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ ሙላቱ አስታጥቄ፣ አስቴር አወቀ፣ ጥላሁን ገሰሰ፣ ወዘተ… ለዛሬው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ መሰረት ከጣሉ በርካታ አርቲስቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።