አብነት አጎናፍር
የጀማመርኩት የነካካሁት ከዛሬ ነገ ይሆናል ያልኩት
ለጎደለኝም ላለኝም ነገር ለማመስገንም ለሚለኝም ቅር
አቤት – ሲነጋ የጨለመ ሌት
ሲፀዳ ያንተም የኔ ቤት
የተሸፈነም ገመና ይገለጣል ገና
አ – አብዬ ብወጋም ችዬ ዛሬን ስለፋ ነገን በተስፋ
ስጨነቅ ላለመጨነቅ ብከፋም ሳልርቅ ላመሌ ስስቅ
አትከልክሉኝ ልናገር – ያንቺም ሀገር ነው የኔ ሀገር
የተዘረፍኩት ልቤን ነው
ከፋኝ ሰው ሲለኝ ቀን ጣለው
ስንቱን ተው ብለሽ ትቻለሁ
ላንቺ ስል ብዙ አጥቻለሁ
አሀሀሀሀ አሀሀሀሀሀ – አሀሀሀሀሀሀ አሀሀሀሀሀሀ (2×)
እም በከርስደህ አትበሉኝ ተወው ናቅ አርገህ
ካጠፋው አርሙኝ አትናገር ግን አትበሉኝ
እም በከርስደህ አትበሉኝ ተወው ናቅ አርገህ
ዝምማ ዝም ነው የሚያስታውስህ ሰው ማነው
አሀሀሀሀሀሀ አሀሀሀሀሀሀ – አሀሀሀሀሀ አሀሀሀሀሀሀ
(አዝ….) የጀማመርኩት ………
አቤት – መከበር ሆኖ በከንፈር
በሆድ ይፍጀው ነገር ማሰር
እያለ እውነት መናገር
በመሸበት ማደር
አ – አብዬ ብወጋም ችዬ አቅም እንዳላጣ ባንቺ ለመጣ
ካቃተን መኖር ተፋቅሮ ሁሌ መባከን ሁሌ እንጉርጉሮ
አትከልክሉኝ ልናገር – ያንተም ሀገር ነው የኔ ሀገር
ያለመናገር ዝምታ
ልጓም ይሆናል ይሉኝታ
ሁሉንም መቻል ከባድ ነው
መብለጥ መበለጥ ልክ አለው
አሀሀሀሀለ አሀሀሀሀሀ – አሀሀሀሀ አሀሀሀሀሀ
እምበከርስደህ ……
ድክም አለኝ ድክኝ ልቤም ከዳው አቅም (2×)
ካልታደሉት በሱ ፀጋ አይገኝም ለካ በፍለጋ
ካልታደሉት በሱ ፀጋ አይገኝም ታማኝ ወዳጅ ለካ
ጉድ ነው – ዘንድሮስ የመጣው ጉድ አፍቃሪ
ጉድ ነው – ተስፋን አሸክሞ ተባራሪ
ጉድ ነው – እምነት ፍቅር እውነት ወዴት ሄደ
ጉድ ነው- ባልታየየሁም መሄድ ተለመደ
ጉድ ነዉ ጉድ ነው ጉድ ነው
ይገርማል የመቻቸቻል ግንብ
ይገርማል ከፈረሰ
ይገርማል እምነት ማተብም
ይገርማል ከተበጠሰ
ይገርማል እንደ ልጅነት
ይገርማል እንደ እቃቀ
ይገርማል ስናስመስል
ይገርማል አለቀ በቃ
አለቀ አለቀ—–አለቀ——-ተጠናቀቀ
አበቃ አበቃ—–አበቃ—–ልክ እንደ እቃ እቃ
(አዝ) ድክም
ጉድ ነው ከሀገር ሰፊው ሆዴ አንጀት በልተሽ
ጉድ ነው ስመሽ ልትከጂኝ በእንባ አጊጠሽ
ጉድ ነው ልል በልል ቁርኝት መላም የለውም
ጉድ ነው ለነበር አይበቃም ያሳለፍነው
ይገርማል እንደ ብረት
ይገርማል ልብ ከዛገ
ይገርማል እንደ ቅጠል
ይገርማል ከጠወለገ
ይገርማል እንደ ልጅነት
ይገርማል እንደ እቃ እቃ
ይገርማል ስናስመስል
ይገርማል አለቀ በቃ
አለቀ አለቀ አለቀ ተጠናቀቀ………….
በሰዓተው ታይረፍድብከ
ፈጠን ስላ ታይዛኝ ብከ
2× አታተድር ዬዎድከ
ጉወ አተዥነም ባት ያተዥከ
ናውደኸሻል ዬወለዱ
ፈያ ባዥ ቲያጋምዱ
ይዝም ምጣ ቲያቲድብከ
በይ ጩኛኝንም አይጨኝከ
በሰዓተው ታይረፍድብከ——–
የኛ ልጅ በርታ አይዘህ እንዳትረታ
የኛ ልጅ በርቺ አይዞሽ እንዳትረቺ
ጎሽ አትገኝ በጥፎዬ
ንበር አግኝም ኩልማዬ
ድረስ ዬቦ ዬቦ በለ
ስኛት በሀገርደ በሸባለ
በሰዓተው ታይረፍድብከ———
ሰባት ጌ ተክስታኔ
ዶቢ መስቃን ተወለኔ
ርገጥ ንርገጥ ንሸልተ
ንጅን አጅን ንሽ
በሰዓተው ታይረፍድብከ————
የኛ ልጅ በርታ አይዞህ እንዳትረታ
የኛ ልጅ በርቺ አይዞሽ እንዳትረቺ
ሰብሽ ሰብምነ ሰብምነ
2× ሰብሽ ሰብምነ ሰብምነ
አትም ታይመካን ጠለው ዘሚዋነ
ኒበላኒ ምድር ሰብምነ
ዘሚዋነ ይጠላም ሰብምነ
ኒበላኒ አፈር እቲተው ይጠላም
ኒበላው ምድር ሰብምነ
ዘሚዋነ ይጠላም ሰብምነ
አለዎት ሰቡኘት ታው ይብልም ይከላም
ዚ እንኬር ይብል ሰው ቲቂ ቢል እግዜርም
ና የኔ ቆንጆ የኔ ጌታ ስትይ ያምርብሻል
ማር ነው ቃልሽ ይጣፍጣል ከምንም ይበልጣል
ምንም ደስ አይለኝም ያላንቺ ለምጄዉ ህይወትን
አይንሽን ካላየሁ አልነቃም ካልሰማሁ ድምፅሽን
የሳቅ ደስታ ምንጩ የኑሮ ጨው ነሽ ማጣፈጫ
ለዚህ ነዉ የለም ያልኩት የሚቆም ካንቺ ጋር ሆኖ አቻ
የኔ ቆንጆ እመቤቴ ህይወትሽ ህይወቴ
2× ልቁም ጎንሽ ካጠገብሽ ልሁን ምገስ ክብርሽ
የኔ ቆንጃ እመቤቴ ህይወትሽ ህይወቴ
ልቁም ጎንሽ ካጠገብሽ ስትወጂኝ ስወድሽ
አዝ—-
ምኞትሽ እንድታይ አምሮብኝ በምርጫሽ ተዉቤ
ቅናት የማያውቅሽ ፍቅር ነሽ የሰላም እርግቤ
በማር አንደበትሽ ስትይኝ ሁሌ እወድሀለሁ
ቀን በቀን በፍቅርሽ የፀዳ ሀር ልብ ይዣለሁ
የኔ ቆንጆ እመቤቴ ህይወትሽ ህይወቴ
2× ልቁም ጎንሽ ካጠገብሽ ልሁን ሞገስ ክብርሽ
የኔ ቆንጆ እመቤቴ ህይወትሽ ህይወቴ
ልቁም ጎንሽ ካጠገብሽ ስትወጂኝ ስወድሽ
አይንሽን መልክሽን ፀጉርሽን ቁመናሽን ብዬ
የለም የመረጥኩት ለብቻዉ ካንቺ ላይ ነጥዬ
ቃል ፊደል የሰዋሁት ስዬ በምናምነው ምዬ
ቸኩዬም አይደለም እውነት ነው ነብስ ነሽ ዉድዬ
የኔ ቆንጆ እመቤቴ ህይወትሽ ህይወቴ
ልቁም ጎንሽ ካጠገብሽ ልሁን ሞገስ ክብርሽ
የኔ ቆንጆ እመቤቴ ህይወትሽ ህይወቴ
ልቁም ጎንሽ ካጠገብሽ ስትወጂኝ ስወድሽ
አሚሊኬኤ ለውተር ጃአሊታአኒ
2× አፍሪሽ ሌክ ዉሩድ ወንዙሙለክ አጋአኒ
አዚፍሌክ ወኦኡዉድ ዊገሪድ ከማኒ
ያ አህለል ዊጁድ ያአህለል አማኒ
ማኩንታ አልወዱድ ሂነይን ኡዋፊ
የሀላክ ሰዱድ ወራከት ተጃፊ
ከምአዉፌት ወኡውድ ሀቤዴ ተሳፊ
አልዬም አታኡድ ዬምፊራሂው ዘፋፊ
አሚሊኬኤ ……
ሚንከሳት መሀና ኡሚን የንቡህ ሀናን
ሚን ፈርዶስ ኡጀና አልዊጀነን አልሂሳን
ኩንታ ናይም ሀያቲ ኡኩንተሙን አዘማን
ኬፍ ሀንሌክ ከሁቢ ኡደማአል አልሀሊሀን
አሚሊኬኤ…..
ናር አልሁብ ናይም ኡሙረልሁብ ሄይሉ
ኦውሾግ አልከቲር ገልቢህም ባህዲሉ
ደርበል ሁብ ጠዊል በራይ ማህበህ ማህሉ
ያአህባብ ዘማን ተአሉ አስ አሉ
አሚሊኬኤ………
ይቅርታ ልበልሽ ውዴ
ባንቺም በኔም ጥፋት ላንዴ
አስቀይሜሻለው ብዬ ስልሽ
ይቅርታዬን ተቀበይኝ ላንዴ ባክሽ
ተቀበይኝ ተቀበይኝ ተቀበይኝ እምቢ አትበይኝ
ተቀበይኝ ተቀበይኝ ይለፍ ካንቺ እምቢ አትበይኝ
ይመለሳል ሁሉም እሺ በይና
ዛሬም ወድሻለው እመኚኝና
አውቄም ሳላውቅም ያስቀየምኩሽን
ይቅር በይኝና ሰላም ልሁን ደህና
ይቅር በይኝና እኔ ልሁን ደህና
ስታዝኚ እኔ እጎዳለው – ተቀበይኝ
በፀፀት እነዳለው – ተቀበይኝ
ቆምያለው ፊትሽ እኔ – ተቀበይኝ
አቅቶኝ ላይሽ ባይኔ – ተቀበይኝ
ተቀበይኝ ተቀበይኝ ተቀበይኝ እምቢ አትበይኝ
ተቀበይኝ ተቀበይኝ ይለፍ ካንቺ እምቢ አትበይኝ
አዝ…. ይቅርታ ልበልሽ ውዴ……
አውቃለው ይገናል ነገር በኔ ላይ
የእድል ነገር ሆኖ ሲሰጠኝ ከላይ
ባልዋልኩበት መዋል እኔን ጎድቶኛል
ይቅር በይኝና ሰላም ልሁን ደህና
ይቅር በይኝና እኔ ልሁን ደህና
እምባሽን ለማበሻ ተቀበይኝ
ባይሆንም መካሻ ተቀበይኝ
ይቅርታዬን በይ አንቺ ተቀበይኝ
የኔ ውድ አታመንቺ ተቀበይኝ
ተቀበይኝ ተቀበይኝ ተቀበይኝ እምቢ አትበይኝ
ተቀበይኝ ተቀበይኝ ይለፍ ካንቺ እምቢ አትበይኝ
አይደለም እንዴ ሃገር ደና
ያስብላል ኧረ የኔስ ፈተና
ያሰብኩት ሁሉም ሲቀር መና
አልፋለው ዛሬም በምስጋና
የኔ ነገር ምን ሆኜ ነው ሰው እያለ ባዶ የማየው
ለምን ይሆን የሚጨንቀኝ የቆምኩበት ያልተመቸኝ
በሰው ሲደርስ የምጠላው እንደገሃነም የምፈራው
ገና ገና ስል ደፋ ቀና
“ “ ሳልም ለገና
“ “ ልኖር ስል ገና
“ “ የሚገጥመኝ ክፉ ፈተና
ገና ገና የህይወት ፈተና
“ “ አይቆምምና
“ “ ቻል ልቤ ጽና
“ “ ከአቅም በላይ አይሰጥምና
አይደለም እንዴ ሃገር ደና
ያስብላል ኧረ የኔስ ፈተና
ያሰብኩት ሁሉም ሲቀር መና
አልፋለው ዛሬም በምስጋና
በጨረቃ ስንት አውግተን ፍቅር ለብሰን ተዋህደን
ትላንት አብረን ነገን ናፍቀን መሃል ዛሬ እየለየን
ሁሉን አውቆስ ተጠንቅቆ ይኖራል ወይ ከሰው ርቆ
ገና ገና ስል ደፋ ቀና
“ “ ሳልም ለገና
“ “ ልኖር ስል ገና
“ “ የሚገጥመኝ ክፉ ፈተና
ገና ገና የህይወት ፈተና
“ “ አይቆምምና
“ “ ቻል ልበ ጽና
“ “ ከአቅም በላይ አይሰጥምና
ሳያት የሆነ ቦታ ድንገት ለአይኔ ሞልታ በአንድ አፍታ
ቆምኩኝ ፍዝዝ ብዬ የት ነው ማውቃት ብዬ ጉዳዬን ጥዬ
ውስጤ ኖሮ ነው ነው ሰበብ
ገጽ አምሳሏ ሰበብ ነው ሰበብ
ደነገጥኩኝ ነው ነው ሰበብ
ሳያት በእውኗ ሰበብ ነው ሰበብ
ሰበብ ነው ሰበብ ነው ሰበብ ነው ሰበብ ነው
ሰበብ ነው ሰበብ ነው ሰበብ ነው ሰበብ ነው
ለሁሉም ነገር አዎ ሰበብ ነው ሁሌም በየእለቱ
ሲያገጣጥም ደሞ ልክ እንደዚ ያውም ካንተ አይነቱ
ለሁሉም ነገር አዎ ሰበብ ነው ሁለም በየእለቱ
ሲያገጣጥም ደሞ ልክ እንደዚ ያውም ካንተ አይነቱ
ለመውደድ ለመጥላትም ሰበብ
ለማግኘት ለማጣትም ሰበብ
ለመብላት ለመጠጣትም ሰበብ
ለመውጣት ለመግባትም ሰበብ
ለማግባት ለመፍታትም ሰበብ
ለመስራት ለማረፍም ሰበብ
ለመውደቅ መነሳተም ሰበብ
ልክ እንደኔና እንዳንተ
ሳያት የሆነ ቦታ ድንገት ለአይኔ ሞልታ በአንድ አፍታ
ቆምኩኝ ፍዝዝ ብዬ የት ነው ማውቃት ብዬ ጉዳዬን ጥዬ
ሰርቷት እንጂ ነው ነው ሰበብ
ለኔ ብሏት ሰበብ ነው ሰበብ
ባጋጣሚ ነው ነው ሰበብ
ያገኘኋት ሰበብ ነው ሰበብ
ለሁሉም ነገር አዎ ሰበብ ነው ሁሌም በየእለቱ
ሲያገጣጥም ደሞ ልክ እንደዚ ያውም ካንተ አይነቱ
ለሁሉም ነገር አዎ ሰበብ ነው ሁለም በየእለቱ
ሲያገጣጥም ደሞ ልክ እንደዚ ያውም ካንተ አይነቱ
ለመውደድ ለመጥላትም ሰበብ
ለማግኘት ለማጣትም ሰበብ
ለመብላት ለመጠጣትም ሰበብ
ለመውጣት ለመግባትም ሰበብ
ለማግባት ለመፍታትም ሰበብ
ለመስራት ለማረፍም ሰበብ
ለመውደቅ መነሳተም ሰበብ
ልክ እንደኔና እንዳንተ
የቀረሽ ይመስለኛል ከቀረሽ እኮ ያመኛል
ዘግይታ ነው አርፍዳ ወይ ደሞ አልፋኝ ሄዳ
ስደረድር ነው ያለሁት
በሰበብ በምክንያት ልቤን ደለልኩት
ትታኝ ቢሆንስ ርቃ ሄዳ
ወይ ደግሞ ምናልባት ሌላ ሰው ለምዳ
የኔ- የኔ ነሽ የኔ ነሽ ብዬ ልመን ወይ
እንደ ሃምሌ ፀሃይ በጭንቅ አንቺን ሳይ
አንድ ቀን ዝንት ዐለም ነው ያልመጣሽ ለታ
ታዘግማለች ምድር መዘወሯን ትታ
ስደረድር ነው ያለሁት
በሰበብ በምክንያት ልቤን ደለልኩት
ትታኝ ቢሆንስ ርቃ ሄዳ
ወይ ደግሞ ምን አልባት ሌላ ሰው ለምዳ
የቀረሽ ይመስለኛል ከቀረሽ እኮ ያመኛል
ዘግይታ ነው አርፍዳ ወይ ደሞ አልፋኝ ሄዳ
የኔ- የኔ ነሽ የኔ ነሽ ያልኩት እስከዛሬ
በየ አደባባዩ ነው ወይ ከንቱ ወሬ
እውነት የኔ ነሽ ወይ አዎ ያንተ ነኝ በይኝ
ከከንቱ ሃሳቤ ከሰበቤ ለይኝ
ስደረድር ነው ያለሁት
በሰበብ በምክንያት ልቤን ደለልኩት
ትታኝ ቢሆንስ ርቃ ሄዳ
ወይ ደግሞ ምን አልባት ሌላ ሰው ለምዳ
ድሬ ድሬ ድሬ ዳዋ
ሐረር ሐረር ሐረር ሰዋ
የሚደረብ የሰው ሸማ
ቢያጣም ቢያገኝ ድምፁ አይሰማ
ድሬ ድሬ ድሬ ዳዋ
ሐረር ሐረር ሐረር ሰዋ
ኢፍቱ ኡርጂ በረዴ ኡማ
ኡማን ኢሽሌ አጃኢቡማ
ኡመተ ቁልቁሉ ኡማ ደዋ ድሬ ዳዋ
ጭምሴ ሂመታ በዳ ደዋ ሐረር ሰዋ
ፈከኘ ተአ ቢየ መራ ድሬ ዳዋ
ኤበ ዋቀዬ ኬና ራብራ ሐረር ሰዋ
ዲልሶትቤ – መረሌ አደዜው – መረሌ
ሂፎትቤ – መረሌ ናመሴው – መረሌ
አጊዚህማ – መራ መራ ሸረፍዜው – መራ መራ
ጌዘምሁም – መረሌ ዲስ ሁሌ – መረሌ
ድሬ ድሬ ድሬ ዳዋ
ሐረር ሐረር ሐረር ሰዋ
የሚደረብ የሰው ሸማ
ቢያጣም ቢያገኝ ድምፁ አይሰማ
ሴናን ሴኑማ አዳን አዱማ ድሬ ዳዋ
አቦ ጃለላ ዱጋን ዱጉማ ሐረር ሰዋ
ሂን ፈፈኬሱ ገራንሳ ፏላ ድሬ ዳዋ
አመለ ቶኮ ኬሰሌ አላ ሐረር ሰዋ
ዲልሶትቤ – መረሌ አደዜው – መረሌ
ሂፎትቤ – መረሌ ናመሴው – መረሌ
አጊዚህማ – መራ መራ ሸረፍዜው – መራ መራ
ጌዘምሁም – መረሌ ዲስ ሁሌ – መረለ
ሞይ አንሌ – ቴቴ ዘሪ ዛኢሂንቴ
ቲ ኤሌም – አረግ ዚቤ ዛ ኢንቴ
ሞይ አንሌ – ዘይዊቄ አትወቂሌ
ቲ ኤሌም – አዘይ ሃረሪ ኢንቴ
ሻህ ቢዜው ራህመቱም ዘሊንቴ
ሀርቱቤ ዘይ ሐደር ቤን
ሁሉቤ ባዴህ ሙሉህ ዚቴንቴ
ይኸው አልተለወጥች ዛሬም አብራኝ አለች
ይኸው አልተቀየረች የልቤን ታውቃለች
እንደልብሽ የኔ አለም የኔ እንደልቤ
መክሊቴ ነሽ ሙሉ ሃሳቤ
በብርሃን ብዛት በሻማዋ ጥላ
እሷ እየቀለጠች ላይኔ ተከልላ
ሰው የለኝም እያልኩ ሳዝን ሳሳዝናት
አለሁ ሳትል ኖራ ክፉ ቃል ሳይወጣት
እንክርት አይኖቿ እንቅልፍ አተው
ሰቀቀን ስስት ተኩለው
ሲነጠቅ ሲጎዳ ስሜቷ
ስታስብ እንዲቆም ቤቷ
በእንቁ ማስቀመጫ በሙዳይ
ደብቃኝ ቋጥራኝ ልቧ ላይ
ድክመቴን ክፍቴን እያየች
ታግሳኝ ሙሉ አርጋኛለች
ነሽ ፀደይ የኔ ሲሳይ የኔ አደይ
ነሽ ፀደይ የኔ ሲሳይ የኔ አደይ
ሁ ላላላ ላላላ ላላላ
ሁ ላላላ ላላላ ላላላ
ይኸው አልተለወጥች ዛሬም አብራኝ አለች
ይኸው አልተቀየረች የልቤን ታውቃለች
እንደልብሽ የኔ አለም የኔ እንደልቤ
መክሊቴ ነሽ ሙሉ ሃሳቤ
ያንን ክፉ ጊዜ ያንን የእሳት ዘመን
መርታኝ አሳልፋኝ በልጣ ከአይኔ ብሌን
አስተምራ አንቅታኝ ለምስጋና አብቅታኝ
ቀኔንና በቴን በአሜን አዘግታኝ
መስከረም ሲጠባ ሲያባራ
አምራ ሳይ የኔን ሙሽራ
እንደ አደይ በቅዬ እንደ አበባ
አቅፋኝ ይዛኝ ስትገባ
ጊዜ አይታ ማትከዳ ማትርቅ
የማትጥል የማትወድቅ
መለወጥ የምትችል የገባት
እንቅፋት የማያስቆማት
ነሽ ፀደይ የኔ ሲሳይ የኔ አደይ
ነሽ ፀደይ የኔ ሲሳይ የኔ አደይ
የቀጠርሽኝ ቦታ እኔ አለው አሃ ሌቦ ነይ
አሁንም እጥብቅሻለው አሃ ሌቦ ነይ
አምንሻለው እወድሻለው አሃ ሌቦ ነይ
እንደማትቀሪብኝ አውቃለው አሃ ሌቦ ነይ
ኣኣ ነይ በይ ነይልኝ ቶሎ ሌባዬ አሃ ሌቦ ነይ
የቆቅ ሆኖልሽል ስጋዬ አሃ ሌቦ ነይ
ሲንኳኳ በራፌ ሲመታ አሃ ሌቦ ነይ
ሲያደነባብረኝ ኮሽታ አሃ ሌቦ ነይ
ክፉ ነገር አጋጥሞሽ አይሆን
የቀረሽው በሰላም ይሁን
በቀጠርሽኝ ቀን ባትመጭም
እኔ አውቃለው አንቺ አትቀሪም
አሃ ሌቦ ነይ አሃሃ ሌቦ ነይ አሃ ሌቦ ነይ አሃሃ ሌቦ ነይ
አምስቱም አምጣት እያሉኝ አሃ ሌቦ ነይ
አስጭነቁኝ እረፍት ነሱኝ አሃ ሌቦ ነይ
ይቀሰቅሱኛል ተኝቼ አሃ ሌቦ ነይ
አው የስመት ህዋሳቶቼ አሃ ሌቦ ነይ
ያ_ቀፈሽ የደበሰሽ እጄ አሃ ሌቦ ነይ
የታለች ይለኛል ወዳጄ አሃ ሌቦ ነይ
በፍቅር የሚያይሽም አይኔ አሃ ሌቦ ነይ
በናፍቆት ደከመልሽ ወይኔ አሃ ሌቦ ነይ
ክፉ ነገር አጋጥሞሽ አይሆን
የቀረሽው በሰላም ይሁን
በቀጠርሽኝ ቀን ባትመጭም
እኔ አውቃለው አንቺ አትቀሪም
ያውቀዋል ድምጽሽን ጆሮየዬ አሃ ሌቦ ነይ
ጠረንሽን አለ አፍንጭዬ አሃ ሌቦ ነይ
መረረው ሁሉም ለምላሴ አሃ ሌቦ ነይ
ከንፈሬን ነከሰብሽ ጥርሴ አሃ ሌቦ ነይ
ኣ ኣ ሳይ ሳገላብጥ ስልኬን ሙሉ ቀን አሃ ሌቦ ነይ
ባትቀሪም ሆንሽብኝ ሰቀቀን አሃ ሌቦ ነይ
ቀልቤንም ህዋሴንም ወስደሽ አሃ ሌቦ ነይ
አታውቂም እንደዚ ቆይተሽ አሃ ሌቦ ነይ
ክፉ ነገር አጋጥሞሽ አይሆን
የቀረሽው በሰላም ይሁን
በቀጠርሽኝ ቀን ባትመጭም
እነ አውቃለው አንቺ አትቀሪም