Support

ሰዋሰው ምን አይነት አገልግሎት ይሰጣል?

በተለያዩ የሀገራችን ተወዳጅ ሙዚቀኞች የተዘፈኑ የሙዚቃ አልበሞችንና ነጠላ ዜማዎችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ማድረስ

የሰዋሰዉን መተግበሪያ እንዴት ማውረድ ይቻላል?

ስልክዎ ላይ Google Play store / App store በመግባት ማዉረድ ይችላሉ👉👉 https://onelink.to/mubp9y

እንዴት የሰዋሰው መተግበሪያ ላይ መመዝገብ ይቻላል?

በመጀመሪያ የሰዋሰውን መተግበሪያ ከጫኑ በኋላ sign in በማለት የሚጠይቀውን መረጃ በመሙላት መመዝገብ ይቻላል

እንዴት የመተግበሪያ ምዝገባ ስህተት መልእክትን ማስተካከል ይቻላል?

ይህንን ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ

የሰዋሰው መተግበሪያ ላይ የአገልግሎት ክፍያን ከፍለን የምናገኛቸው ተጨማሪ ጥቅሞች ምንድናቸው?

● በመረጡት የጥቅል አማራጭ ያልተገደበ የሙዚቃ አገልግሎት ።
● ያሻዎትን የሙዚቃ ምርጫ አውርደው ማዳመጥ ።
● በመረጡት የጥቅል አማራጭያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ያወረዱትን የሙዚቃ ምርጫ offline ማዳመጥ ።
● የራስዎን የሙዚቃ ስብስብ(playlist) መፍጠር ።

ከላይ የጠቀስናቸውን የክፍያ ጥቅል(እለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ እና አመታዊ)የአገልግሎት ጥቅም የምናገኘው በመረጥናቸው የጥቅል አገልግሎት ጊዜ ነው ።
ምሳሌ-እለታዊ የክፍያ ጥቅል ተጠቃሚ ከሆንን የምናገኛቸው አገልግሎቶች:-
● የእለታዊ ያልተገደበ የሙዚቃ አገልግሎት ።
● የእለታዊ የሙዚቃ ምርጫ አውርደው ማዳመጥ ።
● የእለታዊ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ያወረዱትን የሙዚቃ ምርጫ offline ማዳመጥ።
● የእለታዊ የራስዎን የሙዚቃ ስብስብ(playlist) መፍጠር ።

የሰዋሰው የክፍያ ዘዴ?

ሰዋሰው መተግበሪያ የተለያዩ የክፍያ ዘዴ አማራጮችን የያዘ ሲሆን በቴሌ ብር ፣ እና በእናት ባንክ መክፈል ይቻላል

የሰዋሰው መተግበሪያ Subscription እንዴት በቴሌ ብር እና በእናት ባንክ መክፈል ይቻላል ?

በዝርዝር የአከፋፈል ሂደቱን ለማየት፣ ይህንን መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ

እንዴት የሰዋሰው መተግበሪያን አገልግሎት ማቋረጥ ይቻላል?

በቴሌብር ወይም እናት ባንክ ምዝገባን ለማቋረጥ በመጀመሪያ ይሄን ማስፈንጠሪያ https://subscription.sewasewmusic.com/ ተጭነው ወደ ምዝገባ ማስተዳደሪያ ድህረ ገፅ በመሄድ አገልግሎቱን በተመዘገቡበት ስልክ ቁጥር እና እንዲሁም በዚኹ ስልክ ቁጥር በሚላክልዎ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የአንድ ጊዜ መገልገያ የይለፍ ቁጥር (OTP) በመጠቀም ወደ ግል ማህደሮ ይግቡ ::
አማራጭ 1: በመቀጠል subscription ከሚለው ጎን cancel የሚለውን በመጫን ማቋረጥ ይችላሉ።
አማራጭ 2: ከተዘረዘሩት የፕሪምየም ምርጫ ካርዶች ስር በጥቁር ቀለም የተለየው ላይ፣ CANCEL የሚለውን ከተጫኑ፣ አገልግሎቱ ይቋረጣል

የደንበኝነት ምዝገባዎን እንዴት በቴሌ ብር ማቋረጥ ይቻላል?

(https://subscription.sewasewmusic.com/ ) ወደ እዚህ ገጽ ከገቡ በኋላ ሁለት ምርጫዎች አሉዎት
1. ወደ profile በመግባት cancel ማለት ይችላሉ
2. የመረጡትን “premium card” “cancel” ማለት ይችላሉ

የደንበኝነት ምዝገባዎን በእናት ባንክ እንዴት ማቋረጥ ይቻላል?

(https://subscription.sewasewmusic.com/ ) ወደ እዚህ ገጽ ከገቡ በኋላ ሁለት ምርጫዎች አሉዎት
ወደ profile በመግባት cancel ማለት ይችላሉ
የመረጡትን “premium card” “cancel” ማለት ይችላሉ

የሰዋሰው መተግበሪያ ፕሮፋይሎን እንዴት ማስተካከል ይችላሉ?

• በመጀመሪያ ወደ መተግበሪያዎ ይግቡ
• ከዚያም በመቀጠል ወደ ‘Profile’ ዉስጥ ገብተው ከላይ በቀኝ በኩል ‘Edit’ የሚለዉን ይጫኑ
• በመቀጠል ወደ የግል መረጃዎን እንደሚከተለው ያስገቡ
• በመጨርሻም ‘save’ የሚለዉን በመጫን ይጨርሱ

የሰዋሰው መተግበሪያ እንዴት በሞባይል ዳታ መጠቀም ይችላሉ?

• በመጀመሪያ ወደ መተግበሪያዎ ይግቡ
• ከዚያም በመቀጠል ወደ ‘Profile’ ዉስጥ ገብተው ‘setting’ የሚለውን ይጫኑ
• በመቀጠል ‘Allow streaming via mobile data’ የሚለውን በማብራት ይጨርሱ

የሰዋሰው መተግበሪያ እንዴት ላይ እንዴት ቋንቋ ማስተካከል ይቻላሉ?

• በመጀመሪያ ወደ መተግበሪያዎ ይግቡ
• ከዚያም በመቀጠል ወደ ‘Profile’ ዉስጥ ገብተው ‘language’ የሚለውን ይጫኑ
• በመቀጠል ‘set languages’ የሚለውን ተጭነው ወደሚፈልጉት ቋንቋ በመቀየር ይጨርሱ

የሰዋሰው መተግበሪያ ድምጽ እንዴት ማስተካከል ይችላሉ?

• በመጀመሪያ ወደ መተግበሪያዎ ይግቡ
• ከዚያም በመቀጠል ወደ ‘Profile’ዉ ስጥ ገብተው ‘setting’ የሚለውን ይጫኑ
• በመቀጠል ‘play back’ የሚለውን ጋር በመሄድ ‘Change setting’ በመሄድ የሚለውን ይጫኑ
• ከዚያም ‘Volume limit’ ጋር በመሄድ ‘Maximum volume’ የሚለውን ወደሚፈልጉት መጠን ማስተካከል ይችላሉ

ሰዋሰው መተግበሪያ ላይ እንዴት “offline” ማጫወት ይችላሉ?

• በመጀመሪያ ወደ መተግበሪያዎ ይግቡ
• የሚፈልጉትን ዘፈን ከዝርዝር ይምረጡ
• ከዚያም በመቀጠል የሚፈልጉትን ዘፈን የ’download’ ምልክት ይጫኑ
• ‘Download to this device’ በማለት ዘፈኖን ያውርዱ
• Wifi እና data እና በማይኖርነት ሰአት አውርደው ማዳመጥ ይችላሉ።

ሰዋሰው መተግበሪያ ላይ እንዴት የራስዎን “Playlist” መፍጠር ይችላሉ?

• በመጀመሪያ ወደ መተግበሪያዎ ይግቡ
• ‘My Music’ ውስጥ በመግባት ‘create’ የሚለውን ይጫኑ
• ከዚያም ፕሌይሊስቱን የሚፈልጉትን ስም ይሰይሙ
• በመቀጠል በመፈለጊያ ሳጥን ውስጥ የሚወዱትን ዘፈን ርዕስ ያስገቡ
• የፈለጉትን ዘፈን ሲያገኙ ዘፈኖን እየመረጡ ወደሰየሙት ‘playlist’ እንዲገባ በማድረግ ይጨርሱ

ሰዋሰው መተግበሪያ ላይ እንዴት ማጫወት ይችላሉ?

• የመተግበሪያው የፊት ገጽ ወይም ላይ ካሉት የአርቲስት ምስሎች መካከል ይጫኑ
• ከዚያም ወደመረጡት የአርቲስት ዘፈን ዝርዝር ይወስዶታል

የሙዚቃ ባለሙያዎች እንዴት ከሰዋሰው ጋር መስራት ይችላሉ?

የሰዋሰው ድህረ ገጽ ላይ በመግባት ይህን ከታች የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተሎች በመከተል በትክክል መሙላት
● Menu የሚለው ዉስጥ ይገባሉ
● For artist የሚለዉን ይመርጣሉ
● Contact us now የሚለውን በመጫን እነዚህን ሲጨርሱ send በማለት የሰዋሰው ቤተሰብ መሆን ይችላሉ

የሰዋሰው መተግበሪያ ችግሮች እንዴት መፍታት ይቻላል?

የሰዋሰው መተግበሪያ የደንበኞች አገልግሎት የስልክ ጥሪ በመደወል ማንኛዉንም መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ
ስልክ ቁጥር
+251907427884
+251973038135