Sityana Teni at sewasew multimedia
Sityana’s music life started as a 14-year-old girl in Welkite’s “Gurague Bahil Kinet”. At the time, the Cultural Center offered training in both sports and the arts. And, having been allowed to participate, she honed her skills with the help of a 10-month course, progressing from singing to herself around the house to a lifelong commitment to music.
Sityana returned to Addis Ababa with her family after graduation and had the opportunity to practice her music in various clubs. She has since relocated to South Africa, where she currently resides.
In 2001, she released her first single. It was released under the title “zm atbel ( ዝም አትበል)” with lyrics and melody were written by Yosef Gebre and masterfully crafted by Kamuzu Kasa.
With feedback from her first album, she released her second single, “yene jegna( ),” in 2005, with lyrics and melody by Habtamu Bogale and music by Samson Gosaye.
She then went straight into album work, and we’ve been working on it for 9 years.
As a result, Sityana released her third single, “Agul Abay( ),” composed by Elias Melka, in 2011. It also aided her in making contacts in the music industry. In 2014, while waiting for the album’s release, she released another single called “Weleba()”
The album “Maneneten(ማንነቴን)” contains 12 songs and revolves around love and social life. a lot of people participated in this album such as
◦ Composition by Elias Melka, Abel Paulos, and Kamuzu Kasa
◦ Melody by Elias Melka, Abinet Agonafr, Surafel Abebe, Jalud Awol, Bisrat Surafel, Anteneh Werash, and Kasahun Eshetu
◦ Lyrics by Elias Melka, Mesele Getahun, Abinet Agonafr, Natnael Girmachew, Wendesen Yehub, Surafel Abebe, kasahun eshetu, and kahnu moges.
Sityana Teni was born in Debrezeit and did grow up traveling and immersing herself in Ethiopian local tales and cultures in a variety of locations with her family, from Gonder to Addis Ababa.
Early Life
Sityana’s music life started as a 14-year-old girl in Welkite’s “Gurague Bahil Kinet”. At the time, the Cultural Center offered training in both sports and the arts. And, having been allowed to participate, she honed her skills with the help of a 10-month course, progressing from singing to herself around the house to a lifelong commitment to music.
Sityana returned to Addis Ababa with her family after graduation and had the opportunity to practice her music in various clubs. She has since relocated to South Africa, where she currently resides.
Career in Music
In 2001, she released her first single. It was released under the title “zm atbel ( ዝም አትበል)” with lyrics and melody were written by Yosef Gebre and masterfully crafted by Kamuzu Kasa.
With feedback from her first album, she released her second single, “yene jegna( ),” in 2005, with lyrics and melody by Habtamu Bogale and music by Samson Gosaye.
She then went straight into album work, and we’ve been working on it for 9 years.
As a result, Sityana released her third single, “Agul Abay( ),” composed by Elias Melka, in 2011. It also aided her in making contacts in the music industry. In 2014, while waiting for the album’s release, she released another single called “Weleba()”
Maneneten Album
The album “Maneneten(ማንነቴን)” contains 12 songs and revolves around love and social life. a lot of people participated in this album such as
◦ Composition by Elias Melka, Abel Paulos, and Kamuzu Kasa
◦ Melody by Elias Melka, Abinet Agonafr, Surafel Abebe, Jalud Awol, Bisrat Surafel, Anteneh Werash, and Kasahun Eshetu
◦ Lyrics by Elias Melka, Mesele Getahun, Abinet Agonafr, Natnael Girmachew, Wendesen Yehub, Surafel Abebe, kasahun eshetu, and kahnu moges.
Music is life. That’s why our hearts have beats ❤️
Ejen Setehu (እጄን ሰጠሁ)
እጄን ሰጠሁ!
ሲያዩት እንደቆዩትና
ሳያውቁ እንደጠሙት
ጣፋጭ ውሃ
ኡህ- ላውራው ዛሬ
ነግሬው ይስማው ዛሬ
ኡህ- ላውጣው ዛሬ
ሁሉን ገላልጨው ይስማ ውስጤን ዛሬ
ኡኡኡኡኡ እእእእእእእእ
እእእእእእእ አአአአአአአአ
ላሳየው ባልፈቅድም እእእእእ
ግልፄን ላንዴም ላፍታ እእእእእ
ልቤን እሱ ወስዶ ሞልቶብኛል ቦታ
ቆየ እኔን ከረታ
እጄን ሰጠሁ እፍፍፍፍፍ
ተማርኬአለሁ ኡህህህህ
ተማርኬአለሁ እእእእእ
ተማርኬአለሁ እህእህእህ
ተማርኬአለሁ
ኡህ -ላውራው ዛሬ
ነግሬው ይስማው ዛሬ
ኡኡ -ላውጣው ዛሬ
ሁሉን ገላልጨው ይስማ ውስጤን ዛሬ
ኡኡኡኡ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡእእእእእእእእ
አአአአአ እእእእእእእእእ
ላሳየው ባልፈቅድም እእእእእእ
ውስጤን ባንዴ ባፍታ እእእእእ
ሁሉም ባይመስለውም
ወስዷል ሁሉን ቦታ
ቆየ እኔን ከረታ እእእእእ ውስጤን ላሳየው በቃ
እእእእእእእ ተማርኬያለሁ
እእእእእእእ እስከማይቀርልኝ ድረስ
እእእእ እጄን ሰጠሁ
እፍፍፍፍ
ኡኡኡኡኡ እእእእ እእእእ አአአአአ
ኡኡኡኡኡኡኡ እእእእእእእ አሃሃሃ
……………………………………………
Zema (ዜማ)
ዜማ !
በሚነዝር እይታው
ተጨምሮ ፈገግታው
እያመንኩት ሰስቼ
አልጠገውም አይቼ
በሚነዝር እይታው
ተጨምሮ ፈገግታው
እያለነው ከጎኔ
አልጠግብ ያለው በቃ አይኔ
አአ አይኔ አ አይኔ
አአ አይኔ አ አይኔ
ይመኙታል እንጂ እያደር ለጎጆ
ትይቶ አይታለፍም እሸት እና ቆንጆ
አጏጉቶ እንደሚገኝ ያውዳመት ዋዜማ
ቀን በቀን ደስታ ነው ጣፋጭ እንደ ዜማ
ዜማ ነው ዜማ – ዜማ
ዜማ ነው ዜማ -ዜማ
መውደድ ገላን – ዜማ
ነዝሮ እሚስማማ- ዜማ
ዜማ ነው ዜማ- ዜማ
ዜማ ነው ዜማ – ዜማ
ፍቅሩም እስከ ነብስ -ዜማ
ጠልቆ እሚሰማ-ዜማ
# አዝማች# እያወቀው ልቤ ያካሉን ተፈጥሮ
ምን ሊያመጣ ይሆን ማማሩንጠርጥሮ
እስካለሜ ማብቂያ የህይወት ዳርቻ
ያርግልሽ በሉልኝ እሱን ለኔ ብቻ
ዜማ ነው ዜማ – ዜማ
ዜማ ነው ዜማ -ዜማ
መውደዱ ገላን -ዜማ
ነዝሮ እሚስማማ -ዜማ
ዜማ ነው ዜማ -ዜማ
ዜማ ነው ዜማ-ዜማ
ፍቅሩም እስከ ነብስ – ዜማ
ጠልቆ እሚስማማ -ዜማ
አአ አይኔ አ አይኔ
አአ አይኔ አ አይኔ ……
Alhedim (አልሄድም)
አልሄድም!
ተጊጦ እንደሚያዝ እንደ እቅፍ አበባ
ከተንከባከብከኝ ስትወጣ ስትገባ
ለፍቅሬ ከታመንክ ወደድኩሽ ካልከኝ
እኔም ያንተው ብቻ ውድ አፍቃሪህ ነኝ
ውድ አፍቃሪህ ነኝ
ያንተው ነኝ
ሆድየ ከታመንክልኝ
ያንተው ብቻ
እንደምየ እንጎቻ
ብቸኝነት ጎኔን ውጤን ከሚያምሰው
ውስጤን ከሚያምሰው
ምን አለ ብሸነፍ ብረታ ላንድ ሰው
ብረታ ላንድ ሰው
ጊዜም ከሚያልፍብኝ ልቤ እየተመኘ
ልቤ እየተመኘ
ፍቅር ፍቅር ያለው ታማኝ ከተገኘ
ታማኝ ከተገኘ
ያዝ ነዋ አመሌን ውስጤን አሳምሬ
እንዳላጣው ስተቴን ለልቤ አስተምሬ
ቀን የጣለውን እሚያነሳው የለምና
ጊዜው ሳይቀድመኝ የኔ ያልኩትን ልያዝና
የወደድኩትን ሲነኩብኝ ፈፅሞ አልወድም
እኔም ያለሱ ከሱ ሌላ የትም አልሄድም አልሄድም አልሄድም ወዴትም አልሄድም
አልወድም አልወድም ከእሱሌላ አልወድም
# አዝማች
ስለነገ ላስብ ልቤን ልገስፀው
ልቤን ልገስፀው
ወዲህ ወዲያ ማለት እስኪ ለማን በጀው ዘመን ተሻጋሪ ከእቅፍ የማይወጣ
ከእቅፍ የማይወጣ
ታማኝ የልብ ወዳጅ አፍቃሪ እንዳላጣ
አፍቃሪም ከመጣ
ያዝ ነዋ አመሌን ዉስጤን አሳምሬ
እንዳላጣው ስተቴን ለልቤ አስተምሬ
ቀን የጣለውን የሚያነሳው የለምና
ጊዜው ሳይቀድመኝ የኔ ያልኩትን ልያዝና
የወደድኩትን ሲነኩብኝ ፈፅሞ አልወድም
እኔም ያለሱ ከሱ ሌላ የትም አልሄድም
አልሄድም አልሄድም ወዴትም አልሄድም
አልወድም አልውድም ከሱ ሌላ አልወድም
##
Manineten (ማንነቴን)
ማንነቴን
ታምሪያለሽ እያሉ ታምር ነሽ በሙሉ
እየሸነገሉን መላልሰው ደለሉን
ማንነቴን ፍጥረት ሂወቴን መዘኑ ውበቴን
ሾሙን ሻሩን ናቁ አከበሩን እንደፈጠሩን
ጉብዝና ላይደል ምን ብጠቁር ምን ብረዝም ያው ስፈጠር ነው መልኬን ሮጨ በእጄ
አልይዝም
ክቡር ሰውነት ተራ ተሸቀጠ
የክብርት ህይወት በብር ተለወጠ
ሺረው ሊሾሙንውቢት አንቺ ነሽ አንደኛ
እንዲያ በይ አሉን ሊሉን ፈጣን አሳበኛ
እኛን አቁመው የሚመዛዝኑ
ይቺ ያቺ እያሉ ቁጭ ብለው ሊዝናኑ
እኛን አሳቀው እኛን ሊያሳዝኑ
ምናችንነው የሚመዛዝኑ
#አዝማች
እግር እጄን ቁመት ፀጉሬን ድምፄን አልመረጥኩም
ትውለደኝ ሀገር እዛም ይቺም ብየ አላልኩም
ሳልጠየቅ ነው ሆኜ እኔ ያገኘሁት
ተወልጄም ነው ወድጄም ያለሁት
ሴት መሆን ወንድነትስ በራስ አቅም የታል
ከመነዘረው ነው የመጣው ማንሳት መጣል
ጥፋት ከኛም ነው ሰንፈናል እኛማ
ውቢት ለመባል ሴቶች ስንሻማ
አይቶ ለሚመኝ እየቀባጠረ
ዳኘሗት ለሚል እያቆማመረ
ክቡር ሰውነት ተራ ተሸቀጠ
የክብርት ህይወት በብር ተለወጠ
………………..
Zeraf Sil (ዘራፍ ስል)
ዘራፍ ስል!
ላዋይ ሰው ብልም ቀሎልኛል
ላዋይ ሰው ብልም ተሽሎኛል
መውደድህ አይበርድ አስክሮኛል
ላዋይ ሰው ብልም ቀሎልኛል
ወይ ጎራ አይል ነገር ወይ አይርቅ ከደጅአፍ
ውይ አይርቅ ከደጅአፍ
እምም ይላል ፍቅርህ ወዲያው ደግሞ ዘራፍ
ወዲያው ደግሞ ዘራፍ
ላዋይ ሰው ብልም ቀሎልኛል
ላዋይ ሰው ብልም ተሽሎኛል
አሃ አሃ አሂ እርም ያላንተ ባድር
ባልጋው ብሎ አልነጋ
አሃ አሃ አሂ ሲያሰኘኝ አደረ
የት ትሆን ከማን ጋ
ወይ እዘን ላአካሌ ወይ ከልቤ ዉጣ
ወይ ከሆዴ ውጣት
ወይ እርጋ ወይ ውጣት
ምን ይሉት እዳ ነው ምን እሚሉት ቅጣት
ምን እሚሉት ቅጣት
ዋስ ጠርቶ ዋስ ማጣት
አሃሃሃ ሀሀ ልቤ አመሉ ሆኖበት
መያዙ ቢያሰንፈኝ
የፍቅር ጉርሻህ ነው ባየር ያንሳፈፈኝ
ባየር ያንሳፈፈኝ
ዘራፍ ስል ጎንህ ያሳረፈኝ
ዘራፍ ስል ውያለው ዘራፍ ስል
ዘራፍ ስል ልብ ያለኝ ይመስል
ዘራፍ ስል ገረመኝ ዘራፍ ስል
ዘራፍ ስል እኔ አንተን ይመስል
አዝማች
አሃ አሃ አሂ ሚስትም ካለህ ፍታ
ባልል አይን አውጥቼ
አስታውቅ የለም ወይ
ባንተው ጤና አጥቼ
ወይ እዘን ላካሌ ወይ ከልቤ ውጣ
ወይ ከሆዴ ውጣት
ወይ እርጋ ወይ ውጣት
ምን ይሉት እዳ ነው ምን እሚሉት ቅጣት
ምን እሚሉት ቅጣት
ዋስ ጠርቶ ዋስ ማጣት
አሃሃሃ ሀሀ ልቤ አመሉ ሆኖበት
መያዙ ቢያሰንፈኝ
የፍቅር ጉርሻህ ነው ባየር ያንሳፈፈኝ
ባየር ያንሳፈፈኝ
ዘራፍ ስል ጎንህ ያሳረፈኝ
ዘራፍ ስል ውያለው ዘራፍ ስል
ዘራፍ ስል ልብ ያለኝ ይመስል
ዘራፍ ስል ገረመኝ ዘራፍ ስል
ዘራፍ ስል እኔ አንተን ይመስል
##
Kenekahu (ከነቃሁ)
ከነቃሁ!
ሲጀመር ዘና ብየ
እኔ እራሴ አይ እዳየ
ምሩን ናፍቆ እያሰሰኝ ጠፋሁ እኔ
ኩሩ እኔ
አዝኖ ሲርቀኝ ጥብቆ
ልቤ ናፈቀው አጥብቆ
ለካስ ሳፈቅረው ጀምሬ
ሳላውቅ ወድጄው ታስሬ
ልክፈል ደሞ አትበለኝ ያንተን ተራ
እንደኔ አትሁን ክፉ አትስራ
አትቁጠርብኝ እዳ
እኔም ባንተ አልጎዳ
ቆየሁኝ ከነቃሁ
ልጅነትን ካበቃሁ
መውደድ ያማል እንዲህ ለካ ጉዳት ባነው ይብቃ
ተቆጨው ዘና ብየ
እኔው እራሴ አይ እዳየ
ምሩን ናፍቆ እያሰሰኝ ጠፋሁ እኔ
ኩሩ እኔ
ከፍቶት ሲርቀኝ በእኔ አዝኖ
አድሮ አቅም አሳጣኝ ልቤ አዝኖ
በእንቁ ማሾፌ ካለፈ
አቅሌ ወደሱ ከነፈ
ልክፈል ደግሞ አትበለኝ ያንተን ተራ
እንደኔ አትሁን ክፉ አትስራ
አትቁጠርብኝ እዳ
እኔም ባንተ አልጎዳ
ቆየሁኝ ከነቃሁ
ልጅነትን ካበቃሁ መውደድ ያማል እንዲህ ለካ
ጉዳት ባንተው ይብቃ
##
Yene Hilm (የኔ ህልም)
የኔ ህልም!
አንተን ስጠራ ቀን ውየ ባድር
አይሰለቸኝም እስካለው በምድር
ስምክን ሳሞግስ ብውልም ባድር
እኔ አይበቃኝም ቃል ብደረድር
ላንተ ብቻ ነው ቀሪው ዘመኔ
ይበልጥ አምራለሁ ስትሆን ከጎኔ
የምር አይመስለኝም ዛሬ
በጣም ከምውድህ ካንተ ጋር መኖሬ
ይኸው ተሳክቷል ምኞቴ
እድለኛ ሰው ነኝ አንተን በማግኘቴ
ሳይህ ደጋግሜ
ለካ አንተ ነህ ህልሜ
የውስጤን መስፈርቱን
አሟልተሀል ስንቱን
የኔ ልብ መፍቻ
ሆኗል ያንተ ብቻ
ማንም ላይገባበት
ምሏል የኔ አንደበት
አንተየ የኔውን ነገርኩ የኔን እውን
ያላንተም አላልም ልቤም እሺ አይልም
አዝማች
ሁሌም መቼም ክፉ አይንካህ
ብዙ ነገሬ ነህ በምንም አልተክህ
ከላይ አንተን ተሸልሜ
እኔነቴን ልስጥህ ባንተ ይጠራ ስሜ
ሳይህ ደጋግሜ………..
………………..
//
Zemenu (ዘመኑ)
ዘመኑ!
ኦ – ፍቅር ልኩ ጠፍቶኛል
እኔ አልያዝ ብሎኛል
ኦ-የት ድረስ ነው ወሰኑ
ግራ አጋባኝ ዘመኑ
ኦ- ፍቅር ልኩ ጠፍቶኛል
ኧረ አልያዝ ብሎኛል
ኦ- ምን ያህል ነው መጠኑ
ግራ አጋባኝ ዘመኑ
ፍቅር ፀጋ ነበር የሰማይ ስጦታ -አ
እኛው አቀለልነው መንዝረን ሺ ቦታ
ዛሬም ውድነቱን ያን ክብሩን ባይለቅም -አ
ባፍ ጠርተነው እንጂ ኖረነው አናውቅም
ያኔም በቁጣው ዘመን
ኖህም አንቺን መርጦሻል
እርጥብ የወይራ ቅጠል
ይዘሽ ተመልሰሻል
አቅም ይስጥሽ ፈጣሪ
ሂጂ እርግቤ ብረሪ
ሂጂ እርግቤ ብረሪ
ሆየ ሆየ ንገሩኝ ላግኘው ፍቅር የት ብየ
ሆየ ሆየ ንገሩን ላግኘው ደሞ ቸኩየ
ኦ- ፍቅር ልኩ ጠፍቶኛል
ኧረ አልያዝ ብሎኛል
ኦ- ምን ያህል ነው መጠኑ
ግራ አጋባኝ ዘመኑ
እስኪ ማን ካንጀቱ ሰው ከልብ ይወዳል -አ
ኧረ በዚ ዘመን ለማመን ይከብዳል
ሁሉም ወደራሱ መመልከት ከቻለ -አ
ከፍቅር በስተቀር መድሃኒት የታለ
እዬብ ብዙ ታግሶ
ፍቅሩን ለጌታ ገልጿል
አብርሃምም ሳይሰስት
ልጁን ሊሰዋ ደርሷል
ለሚያኖረን ፈጣሪ
እኛስ ነን ወይ አፍቃሪ ዘመንን ተሻጋሪ
ለሚያኖረን ፈጣሪ
እኛስ ነን ወይ አፍቃሪ የውነት ከልብ አፍቃሪ
ሆየ ሆየ ላ………………………………………….
……………………………..
//
Yihun Dehna (ይሁን ደህና)
ይሁን ደህና!
ልንገርሽ ካለ እባክሽ ካለ ስሚኝ ካለ አድምጪኝ ካለ ስከኚ ካለ አትራቂ ካለ
አንዴ ልስማው እሺ ጆሮ ልስጠው በቃ
አልገባኝ እንዳይሆን ይብቃኝ ልረጋጋ
ተፀፅቶስ ቢሆን ማሪኝ ቢለኝና
ብምረው ምን አለ ይሁን ይሁን ደህና
ካለፈስ ቢቆጨኝ ከምል ምን ሆንኩና
መታገስ ሰላም ነው ይሁን ይሁን ደና
ብዘገይ ለደጉ ድንገት አላረጅም
ኩርፍ ጥድፍ እማ ለማንም አይበጅም
ልቡን ልወቅ እንጂ ልቤን እሰጣለው
ይንገረኝ ሁሉን እሺ አደምጣለው
ከንቱ አይከሰርም ለጥል ካልተሮጠ
ፍቅርማ ትርፍ አለው ጊዜ ከተሰጠ
ልቡን ልወቅ እንጂ ልቤን እሰጣለሁ
ይንገረኝ ሁሉን እሺ አደምጣለሁ
ልንገርሽ ካለ እባክሽ ካለ ስሚኝ ካለ
አድምጪኝ ካለ ስከኚ ካለ አትራቂ ካለ
አንዴ ልስማው እሺ ጆሮ ልስጠው በቃ
አልገባኝ እንዳይሆን ይብቃኝ ልረጋጋ
ተፀፅቶስ ቢሆን ማሪኝ ቢለኝና
ብምረው ምን አለ ይሁን ይሁን ደና
ካለፈስ ቢቆጨኝ ከምል ምን ሆንኩና
መታገስ ሰላም ነው ይሁን ይሁን ደና
አንዴ ልስማው እሺ ጆሮ ልስጠው በቃ
አልገባኝ እንዳይሆን ይብቃኝ ልረጋጋ
ሰው አጥፍቶም ቢሆን ምንም ባያበጅ
ፀፅቶት ሲመለስ ና ይባላል እንጂ
ካለፈስ ቢቆጨኝ ከምል ምን ሆንኩና
መታገስ ሰላም ነው ይሁን ይሁን ደና
ተፀፅቶስ ቢሆን ማሪኝ ቢለኝና
ብምረው ምን አለ ይሁን ይሁን ደና
ካለፈስ ቢቆጨኝ ከምል ምን ሆንኩና
መታገስ ሰላም ነው ይሁን ይሁን ደና
ተፀፅቶስ ቢሆን ማሪኝ ቢለኝና
………………………………………
ካለፈስ ቢቆጨኝ………………..
…………………………………….,,,,,,
ተፀፅቶስ ቢሆን …………………………..
………………………………………………..
ካለፈስ ………………………………………
………………………………………………….
ተፀፅቶስ ቢሆን ……………………………..
…………………………………
……………………
…………….//
//
Jemamerew (ጀማመረው)
ጀማመረው !
አይወዱ ወድጄው ስኖር ባአመኔታ
እንዳሻው ይሆናል ያላንዳች ይሉኝታ
ጥፋቱን እንዳላየ ለመሆን እስክሞክር
ይዟችሁ ያውቃል ወይ እንዲህ አይነት ፍቅር
ጀማመረው*4
ለሱ መታመኔን ሲገባው ሲረዳ
ይጫወታል በኔ ሁሌ አራዳ አራዳ
ባይኑ እያባበለኝ በሚማርክ ቃሉ
ይኸው ጀማመረው ሊዋሽ እንዳመሉ
ጀማመረው *2 ፍቅርን ባፉ ሊያሳምረው
ጀማመረው *2 ለመወደድ የፈጠረው
ጀማመረው *2 ፍቅርን ባፉ ሊያሳምረው
ጀማመረው *2 ጀማመረው አሃ
ጀማመረው*2 ለመወደድ የፈጠረው
ጀማመረው*2 ጀማመረው አሃ
እዝማች
ሁሉንም ዘርዝሬ ልወቅሰው ስነሳ
አንዳች ነገር አለው ስቆ የሚያስረሳ
ውስጤ በትንሹ ስንቱን ተቀይሞ
የሱ ትልቅ ጥፋት አይከብደኝም ደግሞ
ጀማመረው*2 ፍቅርን ባፉ ሊያሳምረው
ጀማመረው *2 ለመወደድ የፈጠረው
ጀማመረው *2 ለመወደድ የፈጠረው
ጀማመረው*2 ጀማመረው አሃ
ሁሌግዝት መሃላ
እስኪ ምን ቀረህ ሌላ
ተው ተው አስብ በሀላ
መቼም አንተን አልጠላ
ሁሌ ግዝት መሀላ
እስኪ ምን ቀረህ ሌላ
ለኔም አስብ በሀላ
መቼም አንተን አልጠላ
//
Ande Ketemale (አንዴ ከተማለ)
አንዴ ከተማለ!
መውደዴ መች ጠፋኝ ባልወስን
ልማል ብየ ባልደርስም
ልግባ ግን የታለ
ፍቅር ትኩስ ሳለ
ወዶ ሰው ባንድ እፍታ
ይሁንታ
በቃኝስ መች አለ
አንዴ ከተማለ
መውጣት ቤት ቀልሶ
አፍርሶ
እንደፈቀድከኝ ወደኸኝ እንደመጣህ
እንደመጣህ
ከፊልም ቢሆን ገብቶኛል ከሁኔታህ
ይህ ውዴታህ
በቅድሚያ ግን ባንድ አፍታ
ሳልወስን ልይህ በርጋታ
በጥድፊያ ግን ይቅር
ኪዳን እንዳንሰብር
የሰው ነብስ ያሞታል
ያስቀጣል
እንቆይ እንይ እስኪ ፋፋ
የውነት ፍቅር በኖ አይጠፋ
አልወቅ እንጂ እኔም የኃላው መልሴን
እርግጥ መልሴን
ግን ፈቅዳሃለች ፈርታ ቋምጣለች ነብሴ
ፈቅዳህ ነብሴ
በቅድሚያ ግን ቃል ፈርታ
አለችኝ እይው በርጋታ
በጥድፊያ ግን ይቅር
ኪዳን እንዳንሰብር
የሰው ነብስ ያሞታል
ያስቀጣል
እንቆይ እንይ እስኪፋፋ
የውነት ፍቅር በኖ አይጠፋ
ልግባ ግን የታለ
ፍቅር ትኩስ ሳለ
ወዶ ሰው ባንድ አፍታ
ይሁንታ
በቃኝስ መች አለ
አንዴ ከተማለ
መውጣት ቤት ቀልሶ
አፍርሶ
ልግባ ግን የታለ
ፍቅር ትኩስ ሳለ
ወዶ ሰው ባንድ አፍታ
ይሁንታ
በቃኝስ መች አለ
አንዴ ከተማለ
መውጣት ቤት ቀልሶ
አፍርሶ
ልግባ ግን የት አለ
ፍር ትኩስ ሳለ
ወዶ ሰው ባንድ አፍታ
ይሁንታ
በቃኝስ መች አለ
…………………….
መውጣት ቤት ቀልሶ
…………..
ልግባ ግን የታለ……..
…………………..
//
Engida (እንግዳ)
እንግዳ!
ቸኩሎ ለመሄድ ለምን መጣህ
አይኔ ላይ ይመጣል ሳቅ ጨዋታህ
ማን ብየ ልፈልግ ከየት ብየ
የድንገት እንግዳ ነህ ስቃየ
በሽታየም አንተ መድሀኒቴም አንተ
እጅህ ላይ ከጣልከኝ ቆየ ሰነበተ
መቼ ነው ምትመጣው ተናገር አንተ ሰው
ደግሜ እንዳገኝህ አይኔን እንዳልወቅሰው
ያን ማራኪ ዜማ የሳቅህን ቃና
ባይነ ህሊናየ ሲመጣ እንደገና
እንደታሰረ ሰው እንደተከለለ
መላወስ አቃታተኝ ልቤ አንተን እያለ
ናናናና ወስደህ ቀልቤን
ናናናና ባየኸው ስቃየን
ናናናና የማን እንግዳ ነህ
ናናናና ስምና ውርቄ ነህ
በልና ናናና ናና በል ና ናናና
በል ና ናናና ናና በልና ናናና
አዝማች
አይተሀል ተብሎ አይን አይወቀስም
አምኖም ለመቀበል ልብ አይታገስም
ባንተ ወይስ በኔ በማን ይፈረዳል
ለኔም ለስሜቴም እንግዴ ሆነሃል
ታይቶ ለመሰወር ያጣደፈህ ደርሶ
አያመጣህም ወይ ወደኔ መልሶ
የሳቁት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል
ባንድ እይታ ብቻ ለካ ሰው ይረታል
ናናናና ወስደህ ቀልቤን ልቤን
ናናናና ባየኸው ስቃየን
ናናናና የማን እንግዳ ነህ
ናናናና ሰምና ወርቄ ነህ
በልና ናናናናና በልና ናናና
በልና ናናናናና በልና ናናና
………………………………….
………………………………….
◦ ስሜ ሲትያና ቴኒ ይባላል ትውልዴ ደብረዘይት ሲሆን እድገቴ ከኅንደር እስከ አ.አ በተለያዩ ቦታዎች ከቤተሰብ ጋር በመዘዋወር የየአካባቢው ወግና ባህል ፍቅር ያሳደገኝ ልጅ ነኝ ….
◦ የሙዚቃ ህይወቴ የጀመረው ገና የ 14 አመት ልጅ ሆኜ በጉራጌ ባህል ኪነት ውስጥ በወልቂጤ ከተማ ነው በጊዜው በትርፍ ጊዜ የተለያዩ የስፖርቶች እና የኪነ ጥበብ ስልጠናዎች ይሰጥ ስለነበር ያንን እድል በማግኘቴ ከእቤት ማንጎራጎር አልፎ በስልጠና በልምምድ ተደግፎ የ10 ወር ኮርስ ወስደን ተመርቀን ከሙዚቃ ጋር በተግባር እና በወረቀት ተዛመድን
◦ ከዚያም ቤተሰቤ እንደገና ወደ አዲስ አበባ በመመለሱ በዛ ሰአት አዲስ አበባ ውስጥ ሙዚቃ ይሰራባቸዋል በሚባልበት አጋጣሚዎች ከክበብ እስከ ክለብ በመሳተፍ ልምድ አዳብር ነበር
◦ ከዚያም እንደገና ከቤተሰብ ጋር ወደ አገረ ሳውዝ አፍሪካ በመሰደድ የእድሜየን ግማሽ የኖርኩ ሲሆን እኔ ግን የሙዚቃው ጥሪቱ ሊያስቀምጠኝ ባለመቻሉ ወደ ሀገሬ በመመላለስ ሙዚቃ እየሰራው እመለስ ነበር እናም…
◦ የመጀመሪያ ሲንግሌን በ2001 አ. ም የዬሴፍ ገብሬ ግጥምና ዜማ የሆነውን እና ካሙዙ ካሳ ቆንጆ አድርጎ ያቀናበረውን ዝም አትበል የተባለውን ሲንግል በመልቀቅ ሀ ብየ ወደ ህዝቡ የመጣው ሲሆን ያን ጊዜ ባገኘኃቸው አስተያየቶች ደግሞ በመታገዝ
◦ 2ኛ ሲንግሌን ሀብታሙ ቦጋለ ግጥሙንና ዜማውን ቅንብሩን ደግሞ ሳምሶን ጎሳየ የተጠበቡበትን የኔ ጀግና የተሰኘውን ሲንግል በ2005 አ.ም የሰራው ሲሆን ከዚያ በሃላ በቀጥታ ወደ አልበም ስራ ውስጥ በመግባት 9 አመት የፈጀ አልበም በመስራት ቆየሁ
◦ እናም በመሃል ሌላ 3ተኛ ሲንግሌን የኤልያስ መልካ ግጥም እና ዜማ እንዲሁም ቅንብር የሆነውን ‘አጉል አባይ’ የተሰኘውን በ2011 ለቅቄ የበለጠ ከሰው ጋር እንድተዋወቅና ብዙ ጠቃሚ አስተያየቶችን እንዳገኝ እረድቶኛል
◦ በመቀጠልም አልበሜ ጥሩ ጊዜ እስኪመጣ በመጠበቅ ላይ እያለ ሌላኛውን ደግሞ ግጥምና ዜማው የብስራት ሱራፌል የሆነውን በወጣቱና በታታሪው ታምሩ አማረ የተቀናበረውን “ወለባ” የተባለውን ሲንግል በ2014 ለቅቄያለሁ
አልበሙ 12 ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን በፍቅር እና በማህበራዊ ህይወት ላይ ያጠነጥናል
◦ የአልበሙም መጠሪያ ማንነቴን ! ይባላል በዚህም አልበም ውስጥ
◦ በቅንብር -ኤልያስ መልካ ,አቤል ዻውሎስ ,እና ካሙዙ ካሳ የተሳተፉበት ሲሆን
◦ በዜማ -ኤልያስ መልካ አብነት አጎናፍር ሱራፌል አበበ ጃሉድ አወል ብስራት ሱራፌል አንተነህ ወራሽ እና ካሳሁን እሸቱ ተሳትፈውበታል እንዲሁም
◦ በግጥም -ኤልያስ መልካ መሰለ ጌታሁን አብነት አጎናፍር ናትናኤል ግርማቸው ወንደሰን ይሁብ ሱራፌል አበበ ካሳሁን እሸቱ እና ካህኑ ሞገስ ተክነውበታል .
1/ እጄን ሰጠሁ
ዜማ/ግጥም
ቅንብር/ሚክስ - @ኤልያስ መልካ
2/ ዜማ
ዜማ - ብስራት ሱራፍኤል
ግጥም - ወንደሰን ይሁብ
ቅንብር/ሚክስ - @አቤል ጳውሎስ
3/ አልሄድም
ዜማ/ግጥም - ካሳሁን እሸቱ
ቅንብር/ሚክስ - @አቤል ጳውሎስ
4/ ማንነቴን
ዜማ /ግጥም
ቅንብር/ሚክስ - @ኤልያስ መልካ
5/ ዘራፍ ስል
ዜማ - አንተነህ ወራሽ
ግጥም - ወንደሰን ይሁብ
ቅንብር/ሚክስ - @አቤል ጳውሎስ
6/ ከነቃሁ
ዜማ/ግጥም
ቅንብር/ሚክስ - @ኤልያስ መልካ
7/ የኔ ህልም
ዜማ - ካሳሁን እሸቱ
ግጥም - መሰለ ጌታሁን
ቅንብር/ሚክስ - @አቤል ጳውሎስ
8/ ዘመኑ
ዜማ - ሱራፍኤል አበበ
ግጥም - መሰለ ጌታሁን
ቅንብር - @ ካሙዙ ካሳ
9/ይሁን ደህና
ዜማ - ግጥም
ቅንብር/ሚክስ - @ኤልያስ መልካ
10/ጀማመረው
ዜማ - ብስራት ሱራፍኤል
ግጥም - መሰለ ጌታሁን
ቅንብር/ሚክስ - @አቤል ጳውሎስ
11/ አንዴ ከተማለ
ዜማ/ግጥም
ቅንብር/ ሚክስ - @ኤልያስ መልካ
12/ እንግዳ
ዜማ/ግጥም - አብነት አጎናፍር
ቅንብር/ሚክስ - @አቤል ጳውሎስ